by voice of fano
በሀይማኖት ሰዎች ተግሳፅም ይሁን በብልፅግና ሆዳደር የብአዴን ካድርዎች የሚደርስ ዛቻ በዚህ አይበገሬ ህዝባዊ ተጋድሎ ተሰሚነትም ሆነ ተቀባይነት እንደሌላቸዉ ለፋኖ ባለዉ ድጋፍ እና አብሮነት አክትሟል። በብአዴኑ በአቶ ይርጋ ሲሳይ ባርነትን የሚሠብክ፣ ተንበርካኪነትን እና ተገዥነትን ባህል ያደረገ ትውልድ ለመፍጠር የተደረገው የረጅም ጊዜ ደባ በዚህ ትውልድ እምቢ ባይነት ተደምስሷል።
ሆኖም ፋኖ በራሱ እቅድ፤ ስትራቴጂና የጊዜ ሰሌዳ የሚንቀሳቀስ ሃይል መሆኑን የብልፅግናን ገዳይ ቡድንን አይቀጡ ቅጣት እየቀጣ በተግባራዊ ምላሽ አረጋግጦላቸዋል። ፋኖ መነሻው የህዝብ በደል፣ መዳረሻው የህዝቡ ነፃነት ያደረገ የህዝብ ልጅ ነዉ።
ኢትዮጵያ ከአባቶቻችን የተረከብናት ሀገር ናት የማስቀጠል ግዴታ አለብን ያለዉ ይርጋ ሲሳይ ሀገርን ማስቀጠል አንተ እንደምትገዛለት ገዳዩ ብልፅግና የገበሬን ሰብል በማቃጠል ሴት እና ህፃናትን በመረሸን ተቋማትን በማፍረስ ሳይሆን እንደ ፋኖ ታሪክን እና ቅርስን በመጠበቅ ለህዝብ ደህንነት ቅድሚያ በመስጠት መሆኑን ልትማር ይገባል ። ድል ለአማራ ፋኖ! ወቅታዊ፤ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት voice of fano መርጫወ ይሁን