በሱዳን በተባባሰው ጦርነት የተገደሉ የበርካቶች አስከሬን ጎዳና ላይ መውደቁ ተዘገበ

 ethiopian human right commussion
October 2023

by voice of fano

ወራት ያስቆጠረው የሱዳን ጦርነት በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ተባብሶ ቀጥሏል በሱዳን ዋና ከተማ ካርቱም እና በአገሪቱ ምዕራባዊ ክልል ዳርፉር ውስጥ ከባድ ውጊያ እየተካሄደ መሆኑን እና በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መገደላቸው ተዘገበ። በሱዳን ጦር ሠራዊት እና በፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ መካከል አዲስ በተቀሰቀሰው እና ሐሙስ ዕለት በተባባሰው ውጊያ ምክንያት በኦምዱርማን ከተማ ጎዳናዎች ላይ አስከሬኖች ወድቀው እንደሚገኙ የዐይን እማኞች ለፈረንሳይ ዜና ወኪል ኤኤፍፒ ተናግረዋል። “ትናንት ሐሙስ ከተካሄደው ውጊያ በኋላ ወታደራዊ የደንብ ልብስ የለበሱ ሰዎች አስከሬኖች በከተማዋ ማዕከላዊ ክፍል በሚገኙ ጎዳናዎች ላይ ወድቀው ይገኛሉ” በማለት አንድ የዐይን እማኝ ተናግሯል። በሱዳን ምዕራባዊ ክፍል በምዕራብ ዳርፉር ግዛት ውስጥ ደግሞ በተካሄዱ ግጭቶች 700 የሚደርሱ ሰዎች መገደላቸውን ዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት (አይኦኤም) መግለጹን ድርጅቱ ያወጣውን መግለጫ በመጥቀስ ሮይተርስ የዜና ወኪል ዘግቧል። መግለጫው ጨምሮም የምዕራብ ዳርፉር ግዛት ዋና ከተማ በሆነችው ኤል ጄኒና ውስጥ ከ300 በላይ የሚሆኑ ሰዎች ደግሞ ውጊያውን ተከትሎ የደረሱበት አለመታወቁን ገልጿል። የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል ሙሉ ሱዳንን እቆጣጠራለሁ አለ3 ህዳር 2023 የዳጋሎ ኃይል የአገሪቱን ጦር ኃይል ከሱዳን ሁለተኛ ትልቋ ከተማ ማስወጣቱ ተገለጸ27 ጥቅምት 2023 አሜሪካ የሱዳን የሲቪሎች ልዑክ በአዲስ አበባ ያደረጉትን ውይይት እደግፋለሁ አለች27 ጥቅምት 2023 በግጭቱ ወቅት የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ ወታደሮች አረብ ያልሆኑ ነዋሪዎችን ኢላማ በማድረግ እና በመግደል የዐይን ምስክሮች የፈጥኖ ደራሽ ኃይሎችን ከሰዋል። በካርቱም የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲም የዐይን እማኞችን መረጃ መሠረት አድርጎ “የፈጥኖ ደራሽ ኃይሎች እና በእነሱ የሚደገፉ ሚሊሻዎች በሚፈጽሙት ከባድ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች መረበሹን” ገልጿል። ነገር ግን ፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ “የጎሳ ግጭት” ብሎ በገለጸው ጥቃት ውስጥ ኃይሎቹ እንዳልተሳተፉ በመግለጽ የቀረበበትን ክስ አስተባብሏል። በአገሪቱ ምዕራባዊ ክፍል ውስጥ እየተባባሰ ያለውን ግጭት በመሸሽ ባለፉት ጥቂት ቀናት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የሱዳንን ድንበር በመሻገር ወደ ጎረቤት ቻድ ተሰደዋል። ከተቀሰቀሰ ወራትን ባስቆጠረው በሱዳን እየተካሄደ ባለው ጦርነት አስካሁን ወደ ስድስት ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች ቀያቸውን ለቀው ለመሰደድ መገደዳቸው ተዘግቧል። ባለፈው ዓመት ሚያዚያ ወር መጀመሪያ ላይ በኃያላኑ የአገሪቱ የጦር ጄኔራሎች በሚመሩት በሱዳን ጦር ሠራዊት እና በፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ መካከል የተቀሰቀሰው ጦርነት ሱዳንን ቀውስ ውስጥ አስገብቷታል። አስካሁን የተኛውም ወገን በጦርነቱ የበላይነትን ያልያዘ ሲሆን፣ ሁለቱ ኃይሎች ዋና ከተማዋን ሱዳንን ጨምሮ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ውስጥ ከባድ ጦርነት እኣካሄዱ ይገኛሉ። ባለፉት ወራት ጦርነት በማቆም ከስምምነት እንዲደረስ አሜሪካ፣ ሳዑዲ አረቢያ፣ አህጉራዊ እና ቀጠናዊ ድርጅት እንዲሁም የአካባቢው አገራት ለማሸማገል ጥረት ቢያደርጉም አስካሁን አልተሳካላቸውም።

የአሜሪካ ፖለቲከኞች እስራኤላውያንን ሻማ በማብራት አሰቡ

 ethiopian human right commussion
October 2023

by voice of fano

የአሜሪካ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት እስራኤላውያንን ሻማ በማብራት አሰቡ የአሜሪካ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት እስራኤላውያንን ሻማ በማብራት አሰቡ አሜሪካውያን ፖለቲከኞች ሐማስ የፈጸመበትን ድንገተኛ ጥቃት አንድ ወር በማስመልከት ሻማ በማብራት እስራኤላውያንን አስበው ዋሉ። የአሜሪካ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በዋሽንግተን ዲሲ ባደረጉት የሻማ ማብራት ሥነ ሥርዓት በሐማስ ጥቃት የተገደሉትን እና ታግተው የተወሰዱትን ሰዎች አስበዋል። ሐማስ ከአንድ ወር በፊት በእስራኤል ላይ ድንገተኛ ጥቃት ፈጽሞ ከ1ሺህ 400 ያላሱ ሰዎችን ገድሎ 240 ሰዎች ማገቱ ይታወሳል። በተቃራኒው የእስራኤል ጦር በወሰደው የአጸፋ እርምጃ በሐማስ የሚተዳደረው ጤና ሚንስቴር ከ10ሺህ 300 በላይ ሰዎች መገደላቸውን አስታውቋል።

እርዳታ እንዲቀርብ በተወሰኑ አካባቢዎች ላይ እስራኤል ጥቃቷን ጋብ ማድረጓ ተነገረ

 ethiopian human right commussion
October 2023

by voice of fano

እስራኤል በጋዛ ላይ ጥቃት መፈጸም ከጀመረችበት ከአንድ ወር በኋላ ሠራዊቷ ለመጀመሪያ ጊዜ ለአራት ሰዓታት የሚቆይ ለሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት ጥቃቱን ጋብ ማድረጉን አስታውቋል። በዚህ ለጥቂት ሰዓታት በሚቆየው ከጥቃት ፋታ የሚገኝበት ጊዜ በጋዛ ከተማ ማዕከላዊ ክፍል ውስጥ በሚገኙ ትላልቅ አካባቢዎች የሚገኙ ነዋሪዎች ውሃ እና ምግብ እንዲያገኙ ያስችላል ተብሏል። ጦርነቱ ከጀመረ አንስቶ ከነበረው የአየር ጥቃት አንጻር ዛሬ ረቡዕ በጋዛ ሰርጥ እና በደቡባዊው ክፍል ውስጥ የተፈጸመው የአየር ጥቃት መጠን ዝቅ ያለ መሆኑ ተዘግቧል። ነገር ግን ረቡዕ ማለዳ ላይ በማዕከላዊ ጋዛ ሰርጥ ዴር አል-ባላህ እና በሌሎች ከተሞች ላይ ያነጣጠሩ የአየር ጥቃቶች ተፈጽመው 40 ሰዎች መገደላቸውን እና በርካቶች መቁሰላቸው ተነግሯል። በሰሜን ጋዛ ውስጥ ውጊያ እየተካሄደ በመሆኑ የተነሳ በሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች አካባቢውን ለቀው በእግራቸው እየወጡ ናቸው። በስምንት ግንባሮች እየተካሄደ ያለው ውጊያ አዝጋሚ መሆኑ የተነገረ ሲሆን፣ የእስራኤል እግረኛ ወታደሮች በጋዛ ከተማ ላይ ከበባቸውን ለማጥበቅ ከከተማዋ በስተምዕራብ ወደሚገኘው ቁልፍ የባሕር ዳርቻ መንገድ እየገፉ ናቸው።