by voice of fano
ተረት ተረት እየሰማን በባንዳ ቡችሎች የምንገዛበት ዘመን አብቅቷል ። እናንተ በምትሏት የተረት ተረትና ምናባዊ ሀገር እናንተ ኑሩባት።
የአማራ ገበሬዎች ማዳበሪያ የሚለምኑባት በግብር ያልተገባ ጫና የድህነት አዘቅት ዉስጥ ገብተዉ ልጆቻቸዉን ለማሳደግ የሚቸገሩባት ፣ እንደ ህዝብ ሳንከበር ጦር የሚመዘዝብን፣ በገፍ የምንታሰርባት ፣ የምንገደልባት ሀገር የለችንም ። የአማራ ህዝብ ይሔን ሁሉ ችግር እና ግፍ ከማሳለፍ ሀገር በማለት የግፍ ቀንበሩን ተሸክሟል። ከዚህ በላይ የሚመጣ ከዚህ የባሰ መከራ እና ችግር አይኖርም። የአማራ ህዝብ መገደልንም መሣደድንም ሁሉንም የመከራ ገፈት አንድ በአንድ ገዳዩ መንግስት ፈፅሞበታል።
ይሔ በደል የቀሰቀሰዉ ትዉልድ ነፃነቱን ሊያዉጅ ሞትን በቃህ ብሎ ሊያስወግድ ነፍጥ አንግቦ ላይመለስ ተነስቷል። እናንተ ዲሞክራሲ የምትሉት እና ሰላም ብላችሁ የምትጮሁለት የአማራ ህዝብ ሳይሞት እና ሳይሳደድ ፍትህ ፍለጋ በራሱ ክንድ ሳይነሳ የት ነበርክ? አሁን ሁሉም ነገር መንገድ እና መስመር ይዞ በጀግናዉ ፋኖ ድል ጫፍ ሲደርስ ሰለ ሰላም ማዉራት ህዝብን መሸንገል እና ማታለል ነዉ ።
አማራ ዛሬም ትናንትም በዙ በደሎችን እያስተናገደ ነዉ ይሔ ሊለወጥ የሚችለዉ በጀግና ልጆቹ ክንድ ገዳዩን የአብይ መንግስት አይቀጡ ቅጣት መቅጣት ሲችል ነዉ እሱንም እያደረገዉ ይገኛል ። ድል ለአማራ ፋኖ! ድል ለአማራ ህዝብ!