የአማራ ጭፍጨፋ ይቁም!!!

 ethiopian human right commussion
May 2024

by voice of fano

በሁለት ቀን ብቻ በሁሉም የአማራ ክልል አካባቢዎች ከ555 በላይ ንፁሃን በግፍ በብልፅግና ሰራዊት ተገለዋል። ይህ ስርዓት እንደ ህዝብ አማራን ለማጥፋት መምጣቱን እስካላቆመ ድረስ እንደ ህዝብ ልንታገለው ይገባል። እኔ ሰላማዊ ነኝ ብሎ ትርጉም አልባ ሞት ከመሞት ይልቅ የፋኖን አደረጃጀት በመቀላቀል የመጣውን ጠላት መመከት ግዴታ ነው። እንደዛ ካልሆነ ጦርነቱ በተራዘመ ቁጥር ጨካኙ ስርዓት ጦርነቱን የማሸነፍ አቅም ባይኖረውም ንፁሃንን መጨፍጨፉን ይቀጥላል። ድል ለተገፋው የአማራ ህዝብ !!



የአማራ አንድነት ማህበር በ UK ተመሰረተ

 ethiopian human right commussion  ethiopian human right commussion  ethiopian human right commussion  ethiopian human right commussion  ethiopian human right commussion
March 2024

by voice of fano

በትናንትናው እለት ማለትም March 16 ከተለያዩ የ Uk ከተሞች የተወጣጡ የአማራ ማህበራት በለንደን በመሰብሰብ የአማራ አንድነት ማህበር በ Uk መስርተዋል አላማው ተበታትነው በየከተማው የነበሩትን የአማራ ማህበራት ወደአንድ በማምጣት ለጋራ አላማ በአንድነት መቆምን ይመለከታል በዝግጅቱም ላይ አስካሁን የነበረው ሂደት እና ወደፊትም ሊኬድባቸው የሚገቡ መንግዶች ላይ ማብራሪያ ተሰቷል በዝግጅቱም በርከት ያለ ሰው የተገኘ ሲሆን የተወሰነውን በምስል አስቀምጠናል


ለመብት መታገል የሚያስከፍለው ዋጋ...

 ethiopian human right commussion
September 2023

by voice of fano

2ይህ በፎቶ የምትመለከቱት ወንድማችን በፈረንሳሀ ሀገር ንዋሪ ነበር በፈረንሳይ ሀገር የሚኖሩ የአማራወች ማህበርም ሀላፊ ወይንም ሰብሳቢ በመሆን የበኩሉን እየሰራ የነበረ ልጂ ነው

ይሁን እጂ ከቅርብ ሳምንታት በፊት አራስ ሚስቱን እና አዲስ የተወለደችውን ህፃን ልጁን ለማየት እንዲሁም ለፕሮሰስ አስፈላጊ የሆነውን የጋብቻ ስነስርአት ለመተግበር ወደ ኢትዮጵያ ሄዶ ነበር

ያሰበው ሁሉ ሳይሳካ በተወለደበት አካባቢ የነበሩ የብልፀግና ካድሬወች ከአውሮፓ ነው የመጣው ለፋኖ ያግዛል ብለው ጥቆማ በመስጠት የአብይ ወታደር ቀጥቅጠው ደብድበውት ሄደው ሲያበቁ በድጋሚ ተመልሰው ያቀፋትን ህፃን በመወርወር እሱን ገለውታል በጣም ነው የሚያሳዝነው አማራነት ይህንን ሁሉ መስዋአትነት ያስከፍላል


ከምሥራቅ አማራ ፋኖ የተሰጠ መግለጫ

 ethiopian human right commussion
October 2023

by voice of fano

ድርቅ በሃገሪቱ እየገባ፣ በማዳሪያ እጥረት ምርት ቀንሶ፣ በመከራ የተመረተው የእህል ማሳና ክምር በአገዛዙ የጦር መሳሪያዎች እየተቃጠለ ነው። አገዛዙ የለኮሰው እብደትና ድንቁርና ወለድ ጦርነት፤ በአብዛኛው የሀገሪቱ ክፍሎች ከቡቃያ በላይ በቅሎ ገበሬ ማረስ ያልቻለበትን ሁኔታ ፈጥሯል። አራሽ መሆን የሚገባው ከማሳው ርቆ በከተሞች እየተንከራተተ ወይም በካምፕ ታጉሮ እርጥባን ጠባቂ ሆኗል። እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ የሃገሪቱ ጠቃላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ግን፤ በሰሞንኛው የፓርላማ ዲስኩሩ “ምርት ከአምናው ዘንድሮ ጨምሯል ሲል" ተደምጧል።

በአብይ አህመድና በአገዛዙ ባለስልጣናት ስለኢኮኖሚ የሚነፋውን ቱልቱላ ሃሰትነት አርሶ አደሩ፣ አርብቶ አደሩና ከተሜው በኑሮው ያውቀዋል። ከአገዛዙ ጋር ተጣብቀው እንደ አልቅት የህዝብ ደም ከሚጠጡ ሹመኞችና ባላሃብቶች በስተቀር፣ ረሃብና ረሃብ የወለደው ጭንቅ የሁሉም የሃገሪቱ ዜጎች እጣ ሆኗል። ይህን ህዝብ የሚያውቀውን ሃቅ ክዶ ስለምርት ማደግ ስለልማት የሚያወራ መሪ አንድም እብድ፣ አንድም ሀገር ለማጥፋት የመጣ መሰሪ ወይም ምንም የማይገባው ዳፍንታም እንጂ ሌላ ምን ይባላል?

ሰላም በብዙ የሃገሪቱ ምድር ተናግቶ፤ የቀረውም ግዛት ሰላሙ በቋፍ ላይ በቆመበት ሁኔታ፤ ሰላም አስከባሪ የሚባሉት አካላት መከላከያው፣ ፖሊሱ ደህንነቱ በመሪዎቹ ንቅዘትና የህዝብን ቁጣ መቋቋም አቅቷቸው በድቡሽት ላይ እንደተሰራ ቤት ውልቅልቃቸው እየወጣ ነው። ይህ አለም እያየው ያለ ሃቅ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ምንም አይደለም። "ኢትዮጵያን ሰላም የሰፈነበት ምድር፣ ሰላም አደፍራሾች በመከላከያው በፖሊሱ በደህንነቱ ሃይል እየተመቱ፣ ሰላም እየሰፈነ ነው" እያለ ሲደሰኩር ይሰማል። የሃገር ህልውና አደጋ ላይ በወደቀበት ሰአት ይህን እውነታ ክዶ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ማንም የማይበግረው ሰራዊት እንዳላው፣ እንደሚያሸንፍ ያወራል። ይህንን ስንሰማ “ጠቅላይ ሚንስትሩ አንድም እብድ፣ አንድም ሀገር ለማጥፋት የመጣ መሰሪ ወይም ምንም የማይገባው ዳፍንታም አለዚያ ከቅዠቱ መንቃት የማይፈልግ እንቅልፋም ነው” እንድንል ያደርገናል።

የህዝብ ብሶትና ምሬት፣ ከሰማይ የእሳት ዝናብ በአብይ የጦር ሃይል ሲወርዳባቸውና እየወረድባቸው ያለውን የሃገሪቱን ድሃ አርሶ አደሮች፣ የትምህርትና የጤና የትራንስፖርትና ሌሎች አገልግሎቶች የተቋረጡባቸውን የገጠር ከተሞች አልፎ በሀገሪቱ ዋና ከተማ በአዲስ አበባ ከየማ ውስጥ መደመጥ ጀመሯል። አራት ኪሎ ደጃፍ ደርሶ የጠቅላይ ሚኒስሩን የቤተመንግስት በር እያንኳኳ ነው። በስራ አጥነት በኑሮ ውድነት መጠበስ የመረረው፣ በጉቦ በአድሎ በአፈና ጀርባው የጎበጠው የአዲስ አበባ ህዝብ፤ በትናንትናው እለት በታላቁ ሩጫ ላይ “ክላሽ አማረን” ያለው ለነጻነቱ የተሻሉን ቀናት ለማምጣት ለመሞት ያለውን ቁርጠኛነት ማሳየቱ ነበር። “ፋኖ እየመጣ ነው” ብሎ ሲዘምር ፋኖ የነጻነቱ፣ የሰላሙ፣ ሰርቶ የመኖር ተስፋውን የሚያለመልም እንደሆነ ያመነ መሆኑን የሚያሳይ ነው። በጠቅላይ ሚስትሩ መናገሻ ከተማ የህዝብ ብሶት በአደባባይ ጎልቶ እየተሰማ፤ ጠቅላዩ የተረጋጋ አገር ካላቸው መሪዎች ተራ ለመታየት ወደ ጀርመን መጓዙ ሰውየው አንድም እብድ አንድም ሀገር ለማጥፋት የመጣ መሰሪ ወይም ምንም የማይገባው ዳፍንታም፣ አለዚያ ከቅዠቱ መንቃት የማይፈልግ እንቅልፋም ነው” ብለን እንድናምን አድርጎናል።

የኢትዮጵያ ህዝብ ከስካሁኑ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ድርጊቶች ተነስቶ ሰውየው ከበሽታው እንደማይድን፣ ንስህ የማይገባ፣ ለመማርም ሆነ ለመታረም ፈቃደኛ እንዳልሆነ፣ ከእንቅልፉ እንደማይነቃ ማመን አለበት። የአማራ ህዝብና የአማራ ፋኖ ይህን ከተረዳ ከርሟል። እኛ የአማራ ፋኖዎች በክልላችንም ሆነ በሃገር ደረጃ የምናየው ሃቅ እያበበ፣ እያማረበት፣ እየተጠናከረ የሚሄድ አገዛዝ ሳይሆን፤ ማድያት እየለበሰ፣ እያስቀየመና እየተሽመደመደ የሚሄድ ስርአት ነው። ወታደሩ ጦርነት ባላበት ቦታ ሁሉ የጥይት ድምጽ የሚያሸብረው፣ መሳሪያውን ጥሎ ለመሮጥ የተዘጋጀ፣ በገፍ እጁን የሚሰጥ እየሆነ እየመጣ ነው። ፖሊሱ በሰለጠነ ማግስት መሳሪያ ይዞ እንደሚጠፋ ነው። የሚደማለት የሚቆስልለት አላማ የለውም። ንጹሃን ዜጎች በአገዛዙ በግፍ እየታሰሩ እየተጨፈጨፉ በረሃባ አለንጋ እየተገረፉ እንደሆነ ነው። በአማራ ክልል የብልጽግና አገዛዝ አብቅቶለታል። ከጥቂት ከተሞች ወጭ አስተዳደሩ ሙሉ በሙሉ ፈርሷል። ሁለተኛ ማንሰራራት እንዳይችል አድርገን እየቀበርነው ነው። የአማራ ፋኖ የሚያስጨንቀው የአማራ ክልል ጉዳይ አይደለም። በቅርቡ ክልሉን ከአብይ አህመድ አገዛዝና ተላላኪዎቹ ሙሉ በሙሉ ነጻ እናወጣለን። የሚያሳስበን የተቀረው የኢትዮጵያ ህዝብ ጉዳይ ነው። የአብይ አገዛዝ ሁሉንም ተራ በተራ ለመሰልቀጥ እየተዘጋጀ ነው። አብይ አህመድ ትናንትና “ትግራይን እንዳይግደረደረን አድርገን ሰብረነዋል። እናንተ አማሮች በነሱ መሳሪያ ይዞ መቆየት ለምን ትጨናቃላቸሁ?” ሲለን ነበር። ይህን በነገረን ማግስት፤ አማራን ተገዳዳሪ እንዳይሆን በሚል ሌላ ቀመር ክልሉን ትጥቅ ለማሰፈታት ከተማና ገጠሩን የጦር አውድማ አድርጎታል። “አማራን መስበር ከቻልኩ፤ ትግራይንና አማራን ያየ” እያልኩ ሌላውን ማስፈራሪያና አስጎንብሶ መግዣ አድርጌ መግዛት እችላለሁ በሚል ስሌት አብይ አህመድ እየተንቀሳቀሰ ነው። አይሳካለትም እንጂ ቢሳካለት ከአማራ በኋላ የስርአቱ በትር ተራ በተራ በሁሉም ላይ ማረፉ የማይቀር ነው። የማይታወቀው ቅደም ተከተሉ ብቻ ነው። ይህ በትር ቀጥሎ የሚያርፈው በአገር ወዳዱ የአፋር ህዝብ ላይ ነው፣ ወይስ ከሱማሌ ክልል አልፎ በሌሎች ክልል ህዝቦች ተወዳጅ በሆነው ሙስጠፌና በሚመራው የሶማሌ ክልል ላይ ነው። ወይንስ ከደቡብ ክልል ወጥቶ ተነጥሎ ክልል የሆነው የሲዳማን ክልል ለመዋጥ ነው። ወይንስ ለጋምቤላ ህዝብ እርሻ የሚያስተምሩ በሚል ሰበብ የኦሮሞ ብልጽግና ካድሬዎችን ማስፈር የጀመረባት ጋምቤላ ነች? ወይስ በአብይ ጀነራሎች ወርቋ የሚዘረፈው ቤንሻንጉል? ወይንስ በጎግል ማፕ ላይ የኦሮሚያ ክልል በሚል እየታዩ ያሉ በርካታ የደቡብ ዞኖችንና ወረዳዎች ህዝቦች ላይ ነው? ወይስ ከተማነቷ ኦሮሚያ የሚባል ነጻ ሃገር ዋና ከተማ ለመሆን እየተደገሰለት ያለችው አዲስ አበባና ህዝቧ ናቸው? የአማራ ፋኖ በተቀረው የኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ሊመጣ የሚችለውን አደጋ ከራሱ ተመክሮ በመነሳት አስቀድሞ መተንበይ ችሏል። በአገዛዙ ፋሽሽታዊ ከስክስ ከመረገጥ ማንም አይተርፍም። አገዛዙ በስሙ የሚነግድበት የኦሮሞ ህዝብም ኦሮሞ በመሆኑ በአብይ አገዛዝ ፋሽታዊ ከስክስ ከመረገጥ ነጻ እንደማይሆን ማወቅ አለበት። እስካሁን የተፈጸመበት በደል ሊያነቃው ይገባል። ለዚህም ነው መላው ኢትዮጵያ ከትግራይ እስከ ሶማሌ፣ ከጋምቤላ እስከ አፋር፣ በገጠር በከተማ የሚኖረው ህዝብ በጋራ ተነስቶ የአገዛዙን እድሜ ለማሳጠር ከአማራ ፋኖ ጎን በመቆም በጋራ መረባበርብ አለበት የምንለው። ኅዳር 10 ቀን 2016 ዓ.ም ምሥራቅ አማራ ፋኖ


በ መጠለያ ጣቢያ የሚገኙ የአማራ ተፈናቃዮች የአማራ ብልፅግና አገዛዝ ግድያ ሊያስፈፅምብን ነው አሉ፡፡

 ethiopian human right commussion
October 2023

by voice of fano

የአማራ ህዝብ በኦነግ ሸኔ ብልፅግና እና በብአዴን የሚደርስበት መሳደድ እና ግፍ እሰከ መጠለያ ጣቢያ ተጠናክሮ ቀጥሏል። ከመጠለያ ጣቢያ የሚገኙ የአማራ ተፈናቃዮች የአማራ ብልፅግና አገዛዝ ግድያ ሊያስፈፅምብን ነው ብለዋል፡፡ በኦሮሚያ ክልል የአብይ ገዳይ ቡድን፣በኦሮሚያ ልዩ ኃይልና በሽብርተኛው አኦነግ ሸኔ ተፈናቅለውና ተዘርፈው በደብረብርሃን መጠለያ ጣቢያ የሚገኙ ተፈናቃዮች ያለ ምንም ዋስትና ወደ መጣችሁበት ተመለሱ መባላችን ለከባድ ስጋት አጋልጦናል ብለዋል፡፡

እኛ አማራ በመሆናችን ብቻ ፣ “ወገኖቻችን ቀብረን ፣ ንብረታችን ተዘርፈን፣ አካላቸው የጎደለ ወገኖቻችን እና ሕይወታችንን ብቻ ይዘን ከገዳዮቻችን በተዐምር አምልጠን የወጣን ሰዎች ነን ያሉ ሲሆን ። አማራ ጠል የሆኑት የአገዛዙ ከድሬዎች ሰጡት በተባለ ምላሽ ደግሞ፤ የተዘረፈባችሁን ንብረት ከዚያው ከቦታችሁ ስትሄዱ እናስመልስላችዋለን፤ የተዘረፋችሁትን ንብረትና ቤተሰቦቻችሁን አስመዝግቡ ማለታቸው ተሰምቷል፡፡

የሞቱ ወገኖቻችን እስካሁን ፍትሕ ባላገኙበትና ሽብርተኛው ቡድን አሁንም እየዘረፈ እና እየገደለ ባለበት ሁኔታ እናንተን በምን እናምናችዋለን? ምንስ አቅም አላችሁ? የሚል ጥያቄ ከተፈናቃዮች በኩል ተደጋግሞ መነሳቱን የመረጃ ምንጮች ጠቁመዋል፡፡ ተፈናቃዮቹ አክለውም፣ መንግሥት ለምን አልሞታችሁም በሚል መልኩ ድጋሚ ለገዳይ ኃይሎች አሳልፎ ሊሰጠን እንደሆነ በተደጋጋሚ መረጃዎች ደርሰውናል ብለዋል፡፡ "ከሽብርተኛው ሸኔ በባሰ መልኩ እኛን ለጥቃት ያጋለጠን የኦሮሚያ መንግሥት ነው።" የሚሉት ተፈናቃዮቹ፣ የአማራ ብልፅግና አመራሮች ለርካሽ የፖለቲካ ትርፍ ግድያ ሊያስፈፅሙብን ይችላሉ በማለት ስጋታቸውን ገልፀዋል፡፡ በሽብርተኛ ቡድን ሰበብ ለዓመታት ከኖሩበት ቀያቸው ተፈናቅለው በደብረብርሃን መጠለያ ጣቢያ የሚገኙ የአማራ ተወላጆች አሁንም አስከፊ ሕይዎትን እያስተናገዱ መሆናቸውን በምሬት ተናግረዋል፡፡ ለዚህ በደል እና እንግልት መፈናቀል እና መሳደድየ የአማራ ፋኖ እየታገለ ያለዉ ድል ለአማራ ፋኖ! ድል ለአማራ ህዝብ! Voice of fano መረጃ