ፈጣን መረጃዎችን ከድህረ ገፃችን ይከታተሉ!!

በለንደን አመነስቲ ኢንተራሽናል ፅህፈት ቤት የነበረው ሰላማዊ ሰልፍ

ቀደም ብሎ በዚሁ ድህረ ገፅ events in uk info በሚለው አማራጭ ውስጥ አንዳሳወቅነው ለንደን በሚገኘው አመነስቲ ኢንተርናሽናል ፅህፈት ቤት ፊት የተደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ቪዲዮ እነሆ በቀጣይም uk ላይ ለሚኖሩ ሰላማዊ ሰልፎች እና ስብሰባዎች በዚሁ ድህረ ገፅ events in uk info በሚለው አማራጭ ውስጥ ያገኛሉ

በተጨማሪም ማንኛውንም ፈጣን መረጃ ለመከታተል ይህን ድህረ ገፅ ይጎብኙ

 ethiopian human right commussion
February 2025

by voice of fano



በምሥራቅ ጎጃም በድሮን ጥቃት ሕፃናትን ጨምሮ 16 ሰዎች መገደላቸውን የዓይን እማኞች እና ቤተሰቦች ተናገሩ

 ethiopian human right commussion
February 2025

by voice of fano

በምሥራቅ ጎጃም በድሮን ጥቃት ሕፃናትን ጨምሮ 16 ሰዎች መገደላቸውን የዓይን እማኞች እና ቤተሰቦች ተናገሩ ጥቃቱ የተፈፀመባቸው ቤቶች የምስሉ መግለጫ,ጥቃቱ የተፈፀመባቸው ቤቶች ከ 5 ሰአት በፊት በአማራ ክልል ምሥራቅ ጎጃም ዞን ትናንት ሐሙስ የካቲት 13/2017 ዓ.ም. ተያይዘው በተሠሩ አራት ቤቶች ላይ በተፈጸመ የድሮን ጥቃት 16 ሰዎች ሲገደሉ 10 ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸውን ቤተሰቦች እና የዓይን እማኞች ለቢቢሲ ተናገሩ።

ጥቃቱ በዞኑ ጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ እነገሽ ቀበሌ (ሐሙስ ገበያ) በተባለች አነስተኛ የገጠር ከተማ ሐሙስ ረፋድ 5፡00 ሰዓት አካባቢ በሦስት ሱቆች እና ሻይ ቤት ላይ መድረሱን ቢቢሲ ያናገራቸው ነዋሪዎች ገልጸዋል።

"[ድሮን] ስትዞረን ነበር" ያሉ አንድ የዓይን እማኝ ጥቃቱ ከደረሰበት ስፍራ በግምት 100 ሜትር ርቀት ላይ እንደነበሩ ጠቅሰው፤ የጥቃቱ ሰለባዎች መንገድ ላይ ሲጫወቱ የነበሩ ህፃናት፣ ገበያተኞች እና ሻይ እየጠጡ የነበሩ ሰዎች ናቸው ብለዋል። "ከፍተኛ ፍንዳታ" መፈጠሩን የሚናገሩት እማኙ፤ ወዲያው "አካባቢውን አቧራው፤ የቤቱ ፍርስራሽ በጭስ" እንዳፈነው እና ድንጋጤ እና ግርግር እንደተፈጠረ ገልፀዋል። ሌላ የዓይን እማኝም በፍንዳታው አካባቢው በአቧራ ጭስ መሸፈኑን ጠቅሰው፤ በስፍራው ለመተያትም አስቸጋሪ እንደነበር ተናግረዋል። በደቂቃዎች ውስጥ ጥቃቱ ወደ ተፈፀመባቸው ቤቶች ደርሰው የቆሰሉ ሰዎችን እንዳወጡ እና አስከሬን እንዳነሱ የተናገሩት ሌላ የዓይን እማኝ "የሚጫወቱ ህፃናት እና ቆርቆሮ ሊገዙ የመጡ ሰዎች ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል" ብለዋል። ከሟቾቹ ውስጥ ሙሉጌታ በለጠ የተባለ የስምንት ዓመት ልጃቸው እንደሚገኝበት የተናገሩ አንድ እናት፤ ልጃቸው ሱቆቹ ደጃፍ ላይ ኳስ እየተጫወተ እያለ ስለመገደሉ ለቢቢሲ በሐዘን ውስጥ ሆነው ተናግረዋል። ጥቃቱ ሲደርስ ተጠራጥረው የአንደኛ ክፍል ተማሪ የነበረው ልጃቸውን ሙሉጌታ ፍለጋ፣ ፍንዳታው ወደ ደረሰበት ስፍራ መሄዳቸውን የተናገሩት እናት "ልጄን ንፁሃኖች [አስከሬን] መሃል እንኩት ብሎ [ሞቶ] አገኘሁት" ብለዋል። ሙሉጌታ ሦስተኛ ልጃቸው እንደሆነ የተናገሩት እናት፣ አብሯቸው የሚኖር ብቸኛ ልጃቸው እንደሆነ ጠቅሰው "ቢያመኝ መድኃኒት ገዝቶ፤ ቡና አፍልቶ፤ ሻይ አፍልቶ የሚታዘዘዝ ልጄ ነው" በማለት በሐዘን በተዘጋ ድምጽ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

በደቂቃዎች ውስጥ ጥቃቱ ወደ ተፈፀመባቸው ቤቶች ደርሰው የቆሰሉ ሰዎችን እንዳወጡ እና አስከሬን እንዳነሱ የተናገሩት ሌላ የዓይን እማኝ "የሚጫወቱ ህፃናት እና ቆርቆሮ ሊገዙ የመጡ ሰዎች ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል" ብለዋል። ከሟቾቹ ውስጥ ሙሉጌታ በለጠ የተባለ የስምንት ዓመት ልጃቸው እንደሚገኝበት የተናገሩ አንድ እናት፤ ልጃቸው ሱቆቹ ደጃፍ ላይ ኳስ እየተጫወተ እያለ ስለመገደሉ ለቢቢሲ በሐዘን ውስጥ ሆነው ተናግረዋል።

ጥቃቱ ሲደርስ ተጠራጥረው የአንደኛ ክፍል ተማሪ የነበረው ልጃቸውን ሙሉጌታ ፍለጋ፣ ፍንዳታው ወደ ደረሰበት ስፍራ መሄዳቸውን የተናገሩት እናት "ልጄን ንፁሃኖች [አስከሬን] መሃል እንኩት ብሎ [ሞቶ] አገኘሁት" ብለዋል። ሙሉጌታ ሦስተኛ ልጃቸው እንደሆነ የተናገሩት እናት፣ አብሯቸው የሚኖር ብቸኛ ልጃቸው እንደሆነ ጠቅሰው "ቢያመኝ መድኃኒት ገዝቶ፤ ቡና አፍልቶ፤ ሻይ አፍልቶ የሚታዘዘዝ ልጄ ነው" በማለት በሐዘን በተዘጋ ድምጽ ለቢቢሲ ተናግረዋል።



ቢቢሲ አማርኛ እንደዘገበው

 ethiopian human right commussion
January 2025

by voice of fano

በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ባለፈው ሳምንት 'ሲኖ ትራክ' በተባለ የጭነት ተሽከርካሪ ላይ በተፈጸመ የድሮን ጥቃት 50 የሚሆኑ ሰዎች እንደተገደሉ የዓይን እማኞች እና የተጎጂ ቤተሰቦች ለቢቢሲ ተናገሩ። ጥቃቱ የደረሰው ዞኑ ዳውንት ወረዳ ውስጥ ባለፈው ሐሙስ ኅዳር 19/2017 ዓ.ም. ቀትር 8፡00 አካባቢ መሆኑን የተናገሩት የአካባቢው ነዋሪዎች የጥቃቱ ሰለባዎች ከተለያዩ ጉዳዮች ወደ ኩርባ ከተማ ሲመለሱ የነበሩ ሰዎች ናቸው ብለዋል። የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ስለ ጥቃቱ ጥቆማ እንደደረሰው እና መረጃ እያሰባሰበ እንደሆነ ለቢቢሲ ተናግሯል። ሐሙሲት የተባለ ገበያ ከሚውልበት ሾጋ አካባቢ ወጣ ብሎ ልዩ ስሙ ሰጎራ በተባለ አካባቢ ጥቃቱ መድረሱንም የዓይን እማኞች ተናግረዋል።




ይህ ቪድዮም ለታሪክ ይቀመጥ💔💔

የአብይ መንግስት እና ወታደሮች የአማራን ህዝብ እንዴት በቤተሰብ ፊት እንደሚገድሉ እና እንደሚደፍሩ ለአለም ህዝብ ልናሳይ ይገባል።

ለወትሮው በድብቅ ወይም ብዙ ሰው በማይኖርበት ቦታ ይደረግ የነበረው የድብደባ እና የመግደል ሕዝብን የማሰቃየት ተግባር አሁን ግን በገሃድ በአደባባይ እየተከናወነ ይገኛል ይህን ተግባር ሁሉም ህዝብ ሊያውግዘው እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ እንዲገነዘበው የማድረግ ሃላፊነት አለበት

January 2025

by voice of fano



የ154 አርሶ አደሮች አመታዊ አዝመራ በድሮን ተቃጠለ‼️

 ethiopian human right commussion  ethiopian human right commussion  ethiopian human right commussion  ethiopian human right commussion  ethiopian human right commussion
January 2025

by voice of fano

በሰሜን ወሎ ዞን ዋድላ ወረዳ 03 ቀበሌ ቤተሆር ላይ ትላንት ንፁሀን ላይ ባነጣጠረ የድሮን ጥቃት የ154 አርሶደሮችን አዝመራ በምታዩት መልኩ ወደ አመድነት ተቀይሯል።



የፕሮፌሰር ዓስራት ወልደየስ ዕጣ ፈንታ‼️

 ethiopian human right commussion  ethiopian human right commussion
December 2024

by voice of fano

በዛሬው ዐለት ታህሳስ 03፣2017 የምክር ቤት አባል የሆኑት አቶ ዮሐንስ ቧያለው እና አቶ ክርስቲያን ታደለ በጠና ታመው ወደ መቅረፅ አጠቃላይ ሆስፒታል ተወስደው ነበር። በምረመራው ላይም አዋሽ አርባ በነበሩበት ወቅት ከባድ የሆነ የሆድ ድርቀት ወይም Constipation አጋጥሟቸው ሰለነበረ ወደ ህክምና እንዲወሰዱ በተደጋጋሚ ቢጠይቁም አማራ ጠል የሆነው የአገዛዙ ስርዐት ለስምንት ወራት ያክል ህክምና በሌለበት በአዋሽ አርባ ማስቃያ አሽጎባቸው ራሱ ባመጣባቸው በሽታ እስከዛሬ ድረስ ህክምና የማግኘት መብታቸውን በፍርድ ቤት ቢፈቀድም አገዛዙ ግን በማን አለብኝነት ከልክሎ በጊዜ ህክምና ባለማግኘታቸው ምክንያት ህመማቸው እየተባበሰ መቶ ዛሬ ህመማቸው ቀዶ ህክምና እንዲያደርጉ አስገድዷቸዋል እና በሚያሳዝን ሁኔታ ቁስላቸው በፉሻ እንደተጠቀለለ ሳይደርቅ በአፋጣኝ ወደ ማጎሪያ ቤት ወስደዋቸዋል። ሆስፒታሉም ከ 3-5 ቀን ባለው መተው ያሉበት ደረጃ እንዲታይ እና ከቀዶ ህክምናው ጋር ተያይዞ የደም መፍሰስ ስለሚያጋጥማቸው በአስቸኳይ ማረሚያ ቤቱ ወደ ሆስፒታሉ እንዲያመጣቸው ደብዳቤ ለማረሚያ ቤቱ ፅፉል።



በታላቁ የለንደን ተቃውሞ ሰልፍ ላይ የተነሱ ፎቶዎች እና ቪዲዎ

 ethiopian human right commussion  ethiopian human right commussion
November 2024

by voice of fano

በዚ የተቃውሞ ሰልፍ ላይ በኢትዮጵያ ያለው አምባገነኑ መንግስት በአማራ ሕዝብ ላይ እያደረሰው ያለው የዘር ጭፍጨፋ እንዲቆም እና ዓለምአቀፉ ማህበረሰብ ይህን ድርጊት በይፋ እንዲያወግዝ የሚጠይቁ መፈክሮች ተሰምተዋል በተለይም አለማቀፍ የሚዲያ ተቁአማት በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን የአማራ የዘር ጭፍጨፋ እንዲዘግቡ ተጠይቁአል




በለንደን የቢቢሲ ዋና መስሪያ ቤት የነበረው የተቃውሞ ሰልፍ

October 2024

by voice of fano

ለንደን ላይ በ October,4 በቢቢሲ ዋና መስሪያ ቤት ተካሂዶ በነበረው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ የተነሳ ቪዲዎ እነሆ

መንግስት ህዝብ ላይ በሚፈጽመው የዘረፋ ተግባር ሂወት እየቀተፈ ይገኛል

 ethiopian human right commussion  ethiopian human right commussion  ethiopian human right commussion
september 2024

by voice of fano

በሰሜን ወሎ በዳውንት ወረዳ የህዝብ አገልግሎት የሚሰጡ አንቡላንሶችን የአገዛዙ ስርዓት ወይም የአብይ አህመድ ጋንግስተሮች ለጦርነት ስለወሰዱት የወረዳውን ሀብት በመዝረፍ የወረዳው ማህበረሰብ የህክምና አገልግሎት እንዳያገኝ በመደረጉ ከ4 በላይ የሚሆኑ ወላድ እናቶች የህክምና አገልግሎት ለማግኘት ወደሚችሉበት ተቋም በሰዓቱ ባለመድረሳቸው ህይዎታቸው አልፏል።

የማይቀርበት ለመላው አማራውያን የተዘጋጀ የውይይት መድረክ በለንደን

August 2024

by voice of fano

በአማራ ፋኖ ትግል የመጀመሪያው ግዙፍ የኮር ሰራዊት ተደራጀ።  ethiopian human right commussion
August 2024

by voice of fano

በዋርካው ምሬ ወዳጆ እና በኮሎኔል ፋንታሁን ሙሀቤ የሚመራው የአማራ ፋኖ በወሎ በቀጣናው ያሉ አምስት ግዙፍ ክፍለጦሮችን አጣምሮ ግዙፍ የሰራዊት ኮር ማደራጀቱን የአማራ ፋኖ በወሎ የአስተዳደር ክፍል ኃላፊ ፋኖ አለምነው መብራቱ ለኢትዮ 251 ሚዲያ ገልጧል።

የአማራ ፋኖ በወሎ ዋና አዛዥ ዋርካው ምሬ ወዳጆ እና የአማራ ፋኖ በወሎ አስተዳደር ክፍል ኃላፊ ፋኖ አለምነው መብራቱ እንዲሁም ሌሎችም የአማራ ፋኖ በወሎ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት የአማራ ፋኖ በወሎ የላስታ አሳምነው ኮር መደራጀቱን የአማራ ፋኖ በወሎ ምክትል የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊና የላስታ አሳምነው ኮር ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ፋኖ ሞገስ አባራው ለኢትዮ 251 ሚዲያ ገልጧል።

ከዚህ በተጨማሪም ከራያ እስከ ውጫሌ፣ ከዳውንት እስከ ሐይቅ የሚንቀሳቀሱ የቀድሞው የምስራቅ አማራ ፋኖ ሰባት ግዙፍ ክፍለጦሮች በሁለት ኮሮች መደራጀታቸውንም የአስተዳደር ክፍል ሃላፊው ፋኖ አለምነው መብራቱ ለኢትዮ 251 ሚዲያ ገልጧል።

ቀሪ በደቡብ ወሎና በምዕራብ ወሎ የሚገኙ ክፍለጦርሮችን ወደ ኮር የማሳደግ ስራዎች እየተሰራ መሆኑን የአስተዳደር ክፍል ሃላፊው ፋኖ አለምነው መብራቱ ለኢትዮ 251 ሚዲያ ገልጧል።

ሀምሌ 25 ቀን 2015 ዓ.ም ዛሬ ኮር ሆኖ የተደራጀው የቀድሞው የላስታ አሳምነው ብርጌድ የቅዱስ ላሊበላ አየር ጣቢያን የተቆጣጠረበት እለት በመሆኑ የድል ቀኑን ለማሰብ ዋርካው ምሬ ወዳጆ በተገኘበት እለቱን ይህን ግዙፍ ኮር ያደራጁበት ቀን ሆኗል። ኢትዮ 251 ሚዲያ


በ #አማራ ክልል ከ27 በላይ የሚሆኑ ‘ሰላማዊ ሰዎች’ “በመንግሥት ኃይሎች” መገደላቸው ተነገረ

June 2024

by voice of fano

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ እና ሰሜን ጎጃም ዞኖች በቀናት ልዩነት “የመንግሥት ኃይሎች” ቤት ለቤትና መንገድ ላይ ‘ሰላማዊ ሰዎችን’ መግደላቸውን የዐይን እማኞችና ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ጥቃቶቹ ሰኞ ሰኔ 17 እና ረቡዕ ሰኔ 19፤ 2016 ዓ/ም መፈጸማቸው የተነገረ ሲሆን፤ በጥቃቶቹም ከ27 በላይ ንጹሃን ሰዎች መገደላቸው ተነግሯል።

በሰሜን ሸዋ ዞን ጣርማ በር ወረዳ ከደብረ ሲና ከተማ ወጣ ብላ በምትገኝ ሾላ ሜዳ በተባለች አነስተኛ የገጠር ከተማ ሰኔ 19 በመንግሥት ኃይሎች ደርሷል በተባለ ጥቃት ቢያንስ 15 ሰዎች መገደላቸውን እና አራት የሚሆኑ ሰዎች መቁሰላቸውን ነዋሪዎች ተናግረዋል።

በከተማዋ ‘አጋም በር መገንጠያ’ በተባለ ሰፈር ጥቃቱ 11፡30 አካባቢ እንደተፈጸመ ለቢቢሲ የተናገሩ አንድ ከጥቃቱ የተረፉ እማኝ፤ በጥቃቱ በአብዛኛው ማዳበሪያ ለመውሰድ ከተለያዩ ቀበሌዎች የመጡ አርሶ አደሮች እንደተገደሉ ገልጸዋል።

“የመንግሥት ኃይሎች” ማሙሽ በተባለ ሻይ ቤት ‘ሻይ ቡና’ እያሉ ነበር የተባሉ ስምንት የሚሆኑ ሰዎችን ቤቱ ውስጥ ገብተው እንደገደሏቸው ተናግረዋል።

በሌላ ተመሳሳይ ጥቃት በክልሉ ሰሜን ጎጃም ዞን ይልማና ዴንሳ ወረዳ አዴት ከተማ በሳምንቱ መጀመሪያ ሰኞ ሰኔ 17፤ 2016 ዓ.ም. 11 ንጹሃን ሰዎች በመንግሥት ኃይሎች መገደላቸውን ነዋሪዎች ተናግረዋል።

አዲስ ስታንዳርድ

በሁለት ሚሊዮን ዶላር የተገዛችው ድሮን ተልኮዋን ሳስፈፀም ተከሰከሰች

 ethiopian human right commussion  ethiopian human right commussion
MAY 2024

by voice of fano

‼እግዚአብሔር ይቀጣል‼️

ድሮውን በተለያዩ የዓለማችን ሀገሮች ጠላትን ለማጥቃት ሲውሉ እንመለከታለን በኢትዮጵያ ግን ዓላማቸው የተለየ ከሆነው ቆይቷል ሰላማዊ ዜጎችና በተለይም ህጻናትና ሴቶች የዚህ ጥቃት ሰለባ መሆናቸው የተለመደ ዜና የሆነ መቷል ሆኖም ዛሬ የተሰማው ዜና ግን ከዚህ የተለየ ነው

በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን አቤደንጎሮ ወረዳ ከቱሉገና ከተማ ወጣ ብሎ ጫንጫ ተብሎ የሚጣራው አካባቢ የአገዛዙ ድሮን ዝቅ ብላ አሰሳ እያደረገች ባለችበት ስዓት ምን አደጋ እንደደረሰባት ለግዜው ባይታዎቅም ከአፈር ተቀላቅላለች ሲሉ የአካባቢው ኗሪዎች ገልፀዋል።

በኢትዮጵያ ለአሜሪካ አምባሳደር የተሰጠ ምላሽ።

የከበረ ሰላምታ ለሁላችሁም!

MAY 2024

by voice of fano

አሁን ስልጣን ላይ ያለው አገዛዝ ወደ ስልጣን ከመጣ እነሆ ስድስት ዓመታት አለፉ። ታዲያ፣ በእነዚህ ስድስት ዓመታት አማራዎች በብሄራቸው ምክንያት ተነጥለው ተፈርጀዋል፣ በክፉ ተጥላልተዋል፣ ተፈናቅለዋል፣ ተጠቅተዋል፣ በጅምላ ተጨፍጭፈዋል። ይህ ሁሉ የሆነው በክልል መንግስታት ብቻ ሳይሆን፣ እንደያውም በበለጠ በሚያሳስብ ደረጃ፣ በፌደራል መንግስቱ ተዋናይነት ነው።

ተመልከቱ፣ ከ 1966ቱ አብዮት ጀምሮ፣ በተለያዩ ብሄር ተኮር ድርጅቶች አማካኝነት አማራዎች በብሄራቸው ምክንያት ላለፉት ሃምሳ ዓመታት ሲጠቁ ኖረዋል። ያለፉትን ስድስት ዓመታት ለየት የሚያደርገው ነገር ፣ የዚህ ብሄር ተኮር ጥቃት ዋና ተዋናይ ራሱ አገዛዙ መሆኑ ነው።

ታዲያ፣ እኛ አማራዎች ይህንን የአገዛዙን ጥቃት ለመከላከል ከመነሳት ውጭ ሌላ አማራጭ አልነበረንም። ከታሪክ መማር አለብን። የዘር ፍጅትን ለመፈፀም አቅም ያለው አካል መንግስት ብቻ ነው፤ በተለይ አክራሪ ብሔርተኛ ሆነው የመንግስትን ስልጣን የያዙ ኃይሎች።

የምንታገለው እንደ ህዝብ የመኖር መብታችንን ለማስከበር ነው። የመኖር መብት ደግሞ የመብቶች ሁሉ መሰረት ነው። ለዚህ ነው ምንም እንኳን የትግላችን የመጨረሻ መቋጫው ፖለቲካ ቢሆንም፣ አሁን ያለን ትግል ከፖለቲካ በላይ የህልውና ትግል ነው እያልን አጥብቀን የምንናገረው።

ስለሆነም፣ እስከአሁን ድርድርን አስመልክቶ ስናራምደው የነበረው አቋም ባለበት የሚቆም ቢሆንም፣ ጥያቄው "በምን መልክ ነው?" የሚል ነው እንጂ፣ በትግሎች ሂደት ድርድር አንዱ የሂደቱ አካል እንደሆነ እንገነዘባለን።

በዚህ በኩል የአሜሪካ መንግስት የአማራን ህዝብ የሚወክለውን ፋኖን እና አገዛዙን ለማነጋገር ሁኔታዎችን ለማመቻቸት እየሞከረ ነው። ይህ ጥረት ፍሬ ሊያፈራ የሚችለው ዋና ዋና የፋኖ አደረጃጀቶች ያቀፈ አንድ የአማራ ፋኖ ድርጅት በመጀመሪያ ሲቋቋም ነው። ይህንን ስራ ለማጠናቀቅ ትንሽ ጊዜ ያስፈልገናል። የአማራን ህዝብ ወክሎ በሙሉ ስልጣን ሊናገር የሚችለው እንዲህ ያለው ድርጅት ብቻ ነው።

የአሜሪካን መንግስት፣ ብሎም የዓለም ዓቀፉ ማህበረሰብ በአጠቃላይ፣ በኢትዮጵያ ውስጥ የዘር ፍጅትን (ጄኖሳይድ) ለመከላከል ስለምታደርጉት ጥረት ምስጋናችን ላቅ ያለ ነው።

ፈጣሪ ከሁላችንም ጋር ይሁን!!

እስክንድር ነጋ፣ የአማራ ፋኖ ህዝባዊ ሠራዊት!


ዛሬ በለንደን ዳውኒግ ስትሬት የተካሄደው ሰላማዊ ሰልፍ

 ethiopian human right commussion
November 2023

ዛሬ በለንደን ዳውኒንግ ስትሪት ላይ ባካሄድነው ሰላማዊ ሰልፍ የእንግሊዝ መንግስት በኢትዮጵያ አማራ ላይ እየተካሄደ ያለውን ጭፍጨፋ እንዲያውቁት እና ለማስቆም የበኩላችሀውን እንዲያደርጉ ተይቀናል






ፋኖ ማን ነው

 ethiopian human right commussion
August 2023

by voice of fano

ፋኖ የሚለው ቃል ልቅ በሆነ መልኩ ‘የነጻነት ታጋይ’ ተብሎ የተተረጎመ ሲሆን በብዙሃኑ አስተሳሰብ የቡድኑ መነሻ ከ1935 እስከ 1941 ዓ.ም ድረስ ጣሊያን ፋሽስት ኢትዮጵያን ከያዘበት ጊዜ አንስቶ ነው።

ይሁን እንጂ ከቅርብ አመታት ወዲ ይህ ስም እንዳዲስ መነጋገሪያ እየሆነ በየ ሚዲያውም በየጊዘው የምንሰማው ሆኗል

ለምን ያላችሁኝ እንደሆነ በተለይ ከቅርብ አመታት ወዲ በ አማራ ላይ እየደረሰ ያለው ዘር ተኮር ጭፍጨፋ የሴቶች መደፈር የህጻናት ሞት እና መፈናቀል እየበዛ እና ሰሚ ስላታ ይህ ያንገበገባችሀው የአማራ ወጣቶች ይህን ድርጊት በመቃወማቸው ለነፃነታቸው የሚታገሉበት ስም ነው

ስለሆነም ፋኖ ማን ነው የሚለውን አጭር ጥያቄ ለመመለስ ፋኖ ማለት ለመላው የአማራ ህዝብ ነፃነት የሚታገል እንዲሁም ለሰፊው የኢትዮጵያ ዝብ ነጻነት የበኩሉን አስተዋኦ የሚያደርግ የአማራ ወጣት ነው




Politics News

Amhara News